‹‹የአባ አብርሃ ሕይወት ጉዞ ከየት እስከ የት?››
የክቡር አባ አብርሀ ባራኪ ስርወ-መሰረት ከኢሮብ እምብርት ይመዘዛል፡፡ ይህንን ማህበረሰብ የሚያስተሳስር አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም በሕዝቡ ዘንድ የሰረፀው የማርያም ፍቅር በሁሉም ነገር ውስጥ እንዲያነሱዋት አድርጓቸዋል፡፡ አዛውንቱም፣ ጎልማሳውም፣ ወጣቱም፣ ህፃኑም ሁሉ የነገሮች ማሰሪያቸው፣ የእውነት መገለጫቸው፣ የፍቅር ትስስራቸው ‹‹ማሪያም ናት›› ዓሊተኒ ማሪያሞ!! ይላሉ ኢሮባዊያን - የአሊቴና ማርያም ድረሽልን እንደማለት ነው፡፡ የማርያም ፍቅር ከኢሮባዊያን ደም ጋር የተዋሀደ፣ ከኑሮዋቸው ጋር የተዛመደ በመሆኑ በሚገጥማቸው ችግርና መከራ በስሟ በርካቶች በአግባቡ ያልተተየበ ወይም ያልተፃፈ ግን ደግሞ ብዙ ተአምራትን አይቷል፡፡
No comments:
Post a Comment